በፓርቲ ውህደት ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተጀመረ

ሀዋሳ፡ ህዳር 24/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) በፓርቲ ውህደት ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ላይ ይፋዊ ውይይት መድረክ የደቡብ ክልል ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል::

በፓርቲ ውህደት ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ላይ ይፋዊ ውይይቱን የከፈቱት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ናቸው::

ውህድ ፓርቲው መላው ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉበትና ሁሉንም በእኩል ዓይን የሚያይ መሆኑን ተናግረው አዲሱ ውህድ ፓርቲ እንዲመሰረት ትልቅ መሰረት የጣለው ደኢሕዴን እንደሆነ ገልፀዋል::

ደኢሕዴን ባለፉት ጊዜያት ከፍተኝ ስኬት ቢያስመዘግብም ድክመቶች እንደነበሩት ጠቁመው በስኬት ጉዞ ወደ ፊት እንዳይቀጥል ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እንደነበሩበት ተናግረዋል ::

ድርጅቱ ይገጠመውን ችግሮች ለማረም የሚያስችል አዲስ እሳቤ እንደሚያስፈልገው ተናግረው ችግሮቻችንን ለመቅረፍ አዲስ ውህድ ፓርቲ በማቋቋም ወደ ስራ መገባቱን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተዘጋጀ ሰነድ በድርጅቱ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
ዘጋቢ: ፋሲል ኃይሉ