የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም UNDP ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ሳውዝ ስታር ሆቴል በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የብሄር እና የሃይማኖት ብዝሀነት አያያዝና አስተዳደር በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የሰላም ኮንፈረስን ሲሆን የደቡብ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሲቲያን እና የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በጋር የሰላም ኮንፈረንሱ መድረኩን በፀሎት ከፍተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርሲቲያን ህብረት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባል ፓስተር ፃድቁ አብዶ “የሃይማኖት ብዝሀነት ከሃይማኖት አስተምሮ” በሚል ርዕሰ ላይ ለኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

የሁሉም ሃይማኖት አስተምሮ ይቅርታን፣ መዋደድን፣ መከባበርን ያስተምረናል፣ ይህን አስተምሮ በተግባር መኖር እንደሚገባ ፓስተር ፃድቁ አብዶ ለተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

የሰላም ኮንፈረንሱ ጥቅምት 11 እና 12 ቀን 2012 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ብሄርና ሃይማኖት ብዝሀነት ከማህበራዊ ሳይንስ ጥናት አንፃር በሚል ርዕስና የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የመልካም አስተዳድር ሁኔታ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አደርጎ በቀጣይ ለሰላም ኮንፈረስ ተሳታፊዎች ይቀርባል ተብሎ ይጠበቀል፡፡
ዘጋቢ፡ ፋሲል ኃይሉ