ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ጋር ተወያዩ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ጋር በክልላዊ ሰላም እና የጸጥታ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ኖቤል በመሸለማቸው ደስታቸውን ገልጸው ለክልላዊ ሰላም የበኩላቸውን እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም የአቋም ለውጥ እና በቅንነት የሰላም እና የአመራርን ዋጋ መገንዘብ ክልላዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማስጠበቅ እንደሚረዳ ተናግረዋል።