የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የአመያ ኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2012 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የግቤ ውሃ 4ኛ ፕሮጀክት የሆነውን የአመያ ኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም ከፕሮጀክቱ ሰራተኞችና ከካምፓኒው ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

የአመያ ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እየተገነባ የሚገኘው በጣሊያኑ ሳሊኒ ኢምፔሪጊሎ ኩባንያ ሲሆን የግድቡ ግንባታ የተጀመረው ከዛሬ 3 ዓመት በፊት ሲሆን የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪም 5 ነጥብ 525 ቢሊየን ዩሮ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሳይት አስተባባሪ ኢንጅነር አባይነህ ጌትነት ለምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሰራተኞችም በፕሮጀክቱ ተቀጥረው መስራት ከጀመሩ ወዲህ በርካታ የልምድ ልውውጥና ክህሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ርስቱ ይርዳውም ሰራተኞቹ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ሁሉ መሰረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለአካባቢው ማህበረሰብ ፕሮጀክቱ እያበረከተ ያለውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ርስቱ ይርዳው አድንቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ