ሀዋሳ፡ ነሐሴ 04/2013 ዓ.ም (ደሬቴድ) "One Nation One Pavilion" በሚል መርህ የሚካሄደው ኤክስፖ ሀገራችንን በተለያየ መልኩ ለማስተዋወቅ ሰፊ እድል የሚፈጥር መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በኤክስፖው ላይ ኢትዮጵያን የሚገልጹ ሙዚቃዎች፤ ባህሎች እና የተለያዩ ሀገራችንን የሚያስታውሱ ቀኖች ተሰይመው ይከበራሉ፡፡ የቡና፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣የብሄራዊ ክብረ-በዓል ቀናቶች እንደሚከበሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ማስፋፊያ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ገልጸዋል፡፡
ኤክስፖው እ.ኤ.አ ከኦክቶበር 01 ቀን 2020 እስከ ኤፕሪል 20 ቀን 2021 ሊካሄድ የነበረ ቢሆን በኮቪድ-19 ዓለማቀፍ በወረርሺኝ ምክንያት ከኦክቶበር 01 ቀን 2021 እስከ ኤፕሪል 31 ቀን 2022 ይካሄዳል፡፡
በኤክስፖው ከተሳትፎ የቀረቡት ሶስት ንዑስ ክፍሎች መካከል (OPPORTUNITY) ዕድል፣ (MOBILITY) ተንቀሳቃሽነት እና (SUSTAINABILITY) ዘላቂነት የሚሉ ይገኙበታል፡፡
ባህልና ቅርሶችን፤ ኢንቨስትመንትን፣ ንግድና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና የምኖረው የኤክስፖው ንዑስ ክፍል (OPPORTUNITY) ዕድል በመሆኑ ሀገራችንም የምትሳተፍበት የኤክስፖው ንዑስ ክፍል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
Land of origins & opportunities በሚል መሪ ቃል ሀገራችን በመሳተፍ በዋናነት ዳያስፖራውን፣ የግሉን ዘርፍ፣ እንዲሁም ክልሎችን እና የባህል አምባሳደሮችን በማካተት የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት፣ ንግድና ቱሪዝም ለማስተዋወቅ እየሰራነውም ማለታቸውን ከየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡