አዲሱ ዘመን ለሀገራችን ሰላምና ብልጽግና በጋራ የምንተጋበት ይሁን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ
ሀዋሳ፡ መስከረም 01/2012 (ደሬቴድ) አዲሱ ዘመን ለሀገራችን ሰላምና ብልጽግና በጋራ የምንተጋበት እንዲሆን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አዲሱ ዘመን 2012 ዓ.ም አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ባስተላለፉበት መልክችት ነው ይህን ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመልእክታቸው፤ በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።
“አዲሱ ዘመን 2012 ለሀገራችን ሰላምና ብልጽግና በጋራ የምንተጋበት ይሁን” ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።