የጡረታ መዋጮ ለበጀት ማሟያ መዋሉ ችግር እንደሚፈጥር ኤጀንሲው አስጠነቀቀ፡፡

ሀዋሳ፡ ጷጉሜ 06/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ ቁጠባን ለግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ በማቅረብ የበጀት ጉድለት ማሟያ ማድረጉን ከቀጠለ መንግሥት ችግር እንደሚገጥመው አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳባ ኦሪያ፤ የመንግስት ሰራተኞች ቁጠባ 76 ቢሊዮን ብር ቢደርስም በገቢ ማስገኛ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ በማዋል ኤጀንሲውን ተጠቃሚ በማያደርግ ሁኔታ ለበጀት ጉድለት ማሟያ እንዲውል መደረጉ ቁጠባው ተዳክሞ መንግሥት ችግር ላይ ሊወድቅ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ በኤጀንሲው የማቋቋሚያ አዋጅ የጡረታ ዕቅድ ቁጠባን በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ በማውጣት ለኢንቨስትመንትና ለቦንድ ሽያጭ እንደሚውል የሚደነግግ ቢሆንም፤ ሚኒስቴሩ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ኢንቨስትመንት ለማካሄድ መመሪያ ባለማውጣቱ በአዋጅ የተሰጠውን ሥራ አልሰራም ሲል ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል፡፡