"ህግና ሥርዓት በማይከተሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ ይወሰዳል" ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ።
ሀዋሳ፡ ጷጉሜ 03/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) ህግና ሥርዓትን ተከትለው በማይንቀሳቀሱ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የትምህርት ማህበረሰብ ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ህግና ሥርዓትን በተገቢው መንገድ ማስከበር የሚያስችል ሰነድ ተዘጋጅቷል።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንዳስታወቁት፣ ካለፉት ዓመታት ችግሮች በመማር፣ የመማር ማስተማሩ ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ለማድረግ እንዲሁም ከህግና ሥርዓት ውጪ የሆኑ ነገሮችን የማረም ሥራ በ2012 የትምህርት ዘመን ይሰራል፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ህግና ስርዓት በማያከብሩ ተማሪዎች፣ መምህራንና የትምህርት ማህበረሰብ ላይ ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።