ሀገር አቀፍ የሰላም ቀን በእግር ጉዞ ተጀመረ፡፡
 
ሀዋሳ፡ ጷጉሜ 02/2011 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመተባባር እያከበረው በሚገኘዉ የሰላም ቀን በእግር ጉዞ፣ የኢትዮጵያ የሰላም ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ የመጣል ፕሮግራም፣ በፖናል ውይይት እና በቲያትርና የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ይከበራል።
 
የበዓሉ አካል የሆነዉ የእግር ጉዞ ዛሬ ጷጉሜ 2/2011 ዓ.ም ሰላምን እተክላለሁ ለሀገሬ በሚል መሪ ሃሳብ ከወሎ ሰፈር አደባባይ እስከ ደንበል ድረስ በፌዴራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ታጅቦ እየተከናወነ ነው።
ምንጭ፡ ኤፍቢሲ