የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 10ኛው ዓለም ዓቀፍ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው።
ዩኒቨርሲቲው 10ኛው ዓለም ዓቀፍ ኮንፈረንሱ ሲያካሄድ በዩኒቨርስቲው ምሁራን የተካሄዱ የተለያዩ የጥናትና ምርምሮች ላይ ውይይት ይደረጋሉ።
ኮንፈረንሱ የዩኒቨርስቲው የምክትል ኘሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ነው የተዘጋጀው።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ኘሬዝዳንት ኘሮፌሰር ታከለ ታደሠን ጨምሮ የዩኒቨርስቲው የቦርድ አባላት፣ምክትል ኘሬዝዳንቶች ፣ዲኖች፣ የዩኒቨርስቲው መምህራን ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዚህ መርሀ ግብር ታድመዋል።
ዘጋቢ - አብደላ በድሩ